• Call Us
  • +251467711112

የትምህርት ኮሌጆች ዲን፣ ምክትል ዲኖች ዉድድር ምልመላና መረጣ ማሰፈጻሚያ ረቂቅ መመሪያ በህዝብ አሰተያየት እንዲሰጥበት ቀረበ

የትምህርት ኮሌጆች ዲን፣ ምክትል ዲኖች ዉድድር ምልመላና መረጣ ማሰፈጻሚያ ረቂቅ መመሪያ በህዝብ አሰተያየት እንዲሰጥበት ቀረበ

መጋቢት 9/2017 ዓ.ም

ትምህርት ኮሌጆች ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲወጡ ብቁና ተነሳሽነት ያላቸውን ዲኖችና ምክትል ዲኖች ግልጽ የሆኑ የውድድር መስፈርቶችን በመጠቀም መምረጥና ማሰማራት በተቋማቱ አጠቃላይ አፈፃፀም ላይ የላቀና ጉልህ አስተዋጽኦ አለው፡፡

ይህን ለማሳካት የትምህርት ኮሌጅ ዲኖችና ምክትል ዲኖች ምልመላ፣ መረጣና ስምሪት ማስፈፀሚያ መመሪያ ማዉጣት አስፈልጓል፤

በዚህ መነሻ በክልሉ ትምህርት ቢሮ በርዕሰ መስተዳድር ምክር ቤት የትምህርት ኮሌጆችን ለማስተዳደር በወጣ ደንብ ቁጥር 38/2017 በአንቀጽ 31 ንዑስ አንቀጽ ሰ) ላይ በተሰጠ ስልጣን መሠረት የትምህርት ኮሌጅ ዲኖችና ምክትል ዲኖች ውድድር፣ ምልመላ፣ መረጣና ስምሪት ማስተግበሪያ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡
 
ቢሮው በረቂቅ መመሪያው ላይ ከባለድርሻ አካላት ግብዓት ለመሰብስብ የሚያስችል ዉይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በተጨማሪም ህዝቡ በረቂቅ መመሪያው ላይ አሰተያያት እንዲሰጥ በማስፈለጉ  (Resource ---> Manual)  ውስጥ በመግባትና ረቂቅ መመሪያውን በማየት ለሚቀጥሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት በዌብሳይታች አስተያየት መስጫ ላይ ግብዓት የሚሆኑ አስተያየቶችን እንድሰጡ እንጠይቃለን።

እናመሰግናለን!!