• Call Us
  • +251467711112

ለትምህርት ዘመኑ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተዘጋጀ ከ7 መቶ 9 ሺህ በላይ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍ ለዞንና ልዩ ወረዳዎች ስርጭት ተደርጓል- ትምህርት ቢሮ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ለ2017 የትምህርት ዘመን ከትምህርት ሚኒስቴር የተረከበውን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተዘጋጀ ከ7 መቶ 9 ሺህ በላይ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍ ለዞንና ልዩ ወረዳዎች ስርጭት መደረጉን አስታወቀ።

ይህም በክልሉ የተማሪዎች መማሪያ መጽሐፍ ጥምርታን አንድ ለሁለት ያደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትልና የትምህርት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስከብር ወልዴ ጠቁመዋል።

በክልሉ የ2017 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር መጀመሩን የገለጹት ኃላፊው ዞኖችና ልዩ ወረዳዎችም መጽሐፉን ለትምህርት ቤቶች በአፋጣኝ ማሰራጨት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

መጽሐፎቹ ከፍተኛ ሀብት ወጥቶባቸው ለረዥም ጊዜያት እንዲያገለግሉ ተብሎ የታተሙ መሆናቸው የገለጹት ኃላፊው መጽሐፎቹ ሲሰራጩም ሆነ ተማሪዎች ሲገለገሉባቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ቢሮው ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ከትምህርት ሚኒስቴር የተረከበውን ከ1 ሚልዮን 116 ሺህ በላይ መጽሐፍት ስርጭት ማድረጉ የሚታወስ ነው።

በይዲድያ ተስፋሁን