ህዳር 16/2017 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በመገኘት አጠቃላይ የመማር ማስተማር ሂደትን ምልከታ አድርገዋል።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በስልጤ ዞን የኸይረንዚ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ፣ የወራቤ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ነው ተዘዋውረው ምልከታ ያደረጉት።
አቶ አንተነህ በትምህት ቤቶቹ ያለውን አጠቃላይ የመማር ማስተማር ሂደትን በተመለከቱበት ወቅት፣ ተማሪዎች ጠንክረው እንዲማሩ በማበረታታት በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑም መክረዋል።
በትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማሩ ሂደት በተጠናከረ መልኩ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል።
በአዲሱ ስርዓት ትምህርት የተዘጋጁ የመማሪያ እና ማስተማሪያ መጽሐፍት ለትምህርት ቤቱ መድረሳቸውንም ተመልክተዋል።
ቢሮው ለ2017 የትምህርት ዘመን ከትምህርት ሚኒስቴር የተረከባቸውን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተዘጋጁ ከ7 መቶ 9 ሺህ በላይ መጽሐፍት ለዞንና ልዩ ወረዳዎች ስርጭት ማድረጉም ተጠቁሟል።
Copyrights 2024. . All Rights Reserved.
Developed by NATNAEL ABATE