የ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት እና የውጤት መግለጫ አድራሻ ይፋ ሆኗል፡፡
ተፈታኞች ውጤታቸውን በሚከተሉት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የውጤት መግለጫ አማራጮች ከጳጉሜ 4 ቀን ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ማወቅ እንደሚችሉ ተገልጿል።
በዚህ መሰረት
1. ፖርታል፡- https://result.eaes.et
2. በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- https://t.me/EAESbot
3. በአጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፡- 6284 ላይ ‘R’ን በማስቀደም የመለያ ቁጥር በማስገባት (ምሳሌ R1234567) መልዕክት በመላክ ተፈታኞች ውጤታቸውን ማወቅ እንደሚችሉ ተገልጿል። ይህ አማራጭ ኢትዮ ቴሌኮም የሚያስከፍለው መደበኛ የSMS ክፍያ እንደሚኖረውም ተጠቅሷል።
ተፈታኞች ከውጤት መግለጫ ፖርታልና ቴሌግራም ቦት ላይ ጊዜያዊ ሰርቲፊኬት ማውረድና ማታም እንደሚችሉም የአገልግሎቱ መረጃ ያመለክታል፡፡
በተጨማሪም ተፈታኞች በውጤት እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ቅሬታ ካላቸው ወደ አገልግሎቱ ቢሮ በአካል መምጣት ሳያስፈልግ ከSMS በስተቀር በውጤት መግለጫ አማራጮቹ ላይ (Compliant) የሚለውን በመጫን የቅሬታቸውን ዓይነት በተዘጋጀ የቅሬታ ፎርም ላይ በትክክል በመሙላት ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።
አገልግሎቱ የቅሬታቸውን ምላሽ ቅሬታቸውን ባቀረቡበት ተመሳሳይ አድራሻ የሚያሳውቅ መሆኑንም አስታውቋል።
Copyrights 2024. . All Rights Reserved.
Developed by NATNAEL ABATE